Archives

Tags

ድንቅ ፍቅሩን አይቻለሁ

መዝሙር 34:8
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ #ቅመሱ #እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
ይህ ቃል ከመፀሀፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የምወደው አብዝቼ የምጠቅሰውም ጭምር ነው። ምን አልባትም በጣም ለብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ ሳላካፍላቸው የቀረሁ አይመስለኝም። ይህ ቃል የኔ ቃል ነው ጌታ ልክ እንደዚህ ነው በዘመናት መካከል ቸርነቱን እያቀመሰ ከቀን ወደ ቀን ወደ እቅፉ እያስጠጋ መልካምነቱን ከትላንት ዛሬ እየገለጠልኝ የበልጥ እንድቀርበው፣ እንዳውቀው፣ እንድወደው  ያደረገኝ። መቅመስ መብላት አይደለም ቅምሻ ሁሌም ትንሽዬ ናት እኔም አሁን አሁን ሳስበው በዚህች ትንሽ ዘመን ውስጥ ከመልካምነቱ ጠገብኩ ከፍቅሩ ረካሁ ስል ደሞ ሌላ ቅምሻ ደሞ ሌላ መገለጥ ደሞ ሌላ ምንጭ ይሰጠኝ እና የድሮውን እየረሳሁ ወደጥልቁ እየገባሁ እንድራመድ ያደርገኛል። እዝቄል በራዕይ እንዳየው ማለት ነው።
አብዛኛውን ግዜ የዘነበ ፣ የተገለጠልኝ ፣ ያወቅኩት ሲመስለኝ እርሱ ግን ሁሉን ነገር የካፍያ ያህል እያደረገው በየእለቱ ፍቅሩን መልካምነቱን ቸርነቱን እንደ ሰማይ ጠል እያፈሰሰልኝ 19 ዓመት ሳልጠግበው ፣ ሳይሰለቸኝ ፣ ከፊቱ ዞር ሳልል አለሁ። ለዚህ ነው ይህቺንም ዝማሬ እጅግ የምወዳት። ስንፍናዬ በጣም ብዙ መዝሙሮችን አላውቅም ግን የተወሰኑቱ ከህይወቴ ጋር ተጋብተው ዘመናትን ሁሉ አሻግረውኛል ስሙ ይባረክ።
Daniel Amdemichael
Daniel Amdemichael
🎶🎶
“ድንቅ ፍቅሩን አይቻለሁ  መጠጊያ ሆኖኝ መድህኔ
ወጀቡ እንዳያንገላታኝ ኢየሱስ ቆሞ ከጎኔ “
🎶🎶
ስለዚህ ዝማሬ እግዚያብሔር ይባርክህ።

ምን አልባት ግን አንድ ሰው ይህቺን አንዲት ብጣቂ ፅሁፍ አንብቦልኝ ከሆነ መልክቴ አንድ ብቻ
ነው …. እርሱም

አንድ ግዜ ብቻ ቅመሱት አንድ ግዜ ብቻ ከህይወት ምንጭ ውሀ ጠጡ ከርሱ ውጪ ሌላ እስሚያስጠላቹህ ድረስ በውስጣችሁ የሚፈስስ ሰላም ታገኛላችሁ።  ከዚህ ሁሉ ዘመን በኃላ መቼም ወሬ ለማድመቅ እና ሀይማኖት ለማስፋፋት ይህን አልፅፍም እርሱ እኮ ከሀይማኖት ያልፋል። እኔ እራሴ እግዚያብሔር የሚባል እንዳለ (about His Existance) የተሰበከልኝ ቀን በልቤ ያልኩት አንድ ነገር ነበር እርሱም “ልሞክረው እሰኪ የእውነት ካለ ጥሩ ከሌለ ግን እተወዋለው ምን አስጨነቀኝ” አይገርምም ለካስ አለ ለካስ ይወደኛል ለካስ ይቀመሳል። ቅድም እንዳልኳችሁ በህይወት ዘመኔ ሙሉ በተለይ በልጅነቴ ወቅቶች አንድም ቀን #ሀይማኖት አሳስቦኝ አያውቅም ከልጅነት እስከ እውቀት ድረስ ሀይማኖተኛ ሆኜም አላውቅም ሀይማኖት ኖሮኝም አያውቅም።  እንደውም በጣም ነው የሚያስጠላኝ። አሁንም ቢሆን ኢየሱስ ሀይማኖት ከሆነብኝ በውነት አልከተለውም። ግን ደሞ እርሱ ሀይማኖት አይደለም
እርሱ #እውነት ነው።
እርሱ #ሰላም ነው።
እርሱ #ፍቅር ነው።
እርሱ የህይወት #እንጀራ ነው።
ማንም እንደ ኢየሱስ ሊወደኝ እንደማይችል አሁን አውቄያለሁ። እኔ ድንቅ ፍቅሩን አይቼአለሁ እርሱ መጠግያ ሲሆነኝ አይቻለው። በውነት ይህንን ስለሚበላ እና ስለሚጠጣ አልልም ጳውሎስ እንዳለው እኮ ነው መጠላትንም መወደድንም አይቻለው፣ ረሀብ እና ጥጋብንም ቢሆን ግጥም አድርጌ። ድሮስ ኢትዮጵያዊ አየደለሁ 🧐🧐. ኢየሱስ ግን ከሁሉ ይበልጣል። በግል ቅመሱት እዩትም።
##ኢየሱስ_ያድናል።
#ኢየሱስ_ይዳቸሀል
#ኢየሱስ_ያድናል_ይታደግማል።

4 Comments

  • Stefan

    October 25, 2014 at 6:00 pm

    At quo quodsi sanctus accumsan. Soleat eligendi corrumpit et vim, cu alterum maluisset mel. Et ignota int gream cum. Eu sit noster dolores. Nam an essent eloquentiam.

    Reply
    • John

      March 12, 2014 at 6:01 pm

      Lorem ipsum dolor sit amet, est te posidonium omittantur, eu eum noster alienum. Cetero euismd liquando ne has, tritani euripidis comprehensam an mel. Id brute graecis vix. Falli viderer splendide cum et, urbanitas argumentum necessitatibus vis.

      Reply
  • Silvia

    November 18, 2014 at 6:15 pm

    Ut exerci consequat cum, in quo nemore viderer luptatum, mei no regione dolorum. Ea per idque simul, in estsit referrentur, epicurei omittantur sed ne. Errem interesset ut est, vim no simul consequat.

    Reply
  • David

    December 12, 2014 at 6:15 pm

    Quod iriure has ex. Ut ferri persequeris duo. Deserunt patrioque ex est, per oportere disputando ad.udiandame suscipiantur an per. Mazim iusto semper ut vel mei ea diam liber.

    Reply

Leave a Reply to Silvia Cancel reply