Archives

Tags

ሁለተኛ_አይለመደኝም

ምንም እንኳን እንደብዙዎች ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በየግዜው እና በተገኘው ምክንያት ሁሉ የሚጋረፉ ወላጆች ባይኖሩኝም ግን (በተለይ ደሞ እኔ ያደኩበት ሰፈር ካሉ ወላጆች አንፃር) አልፎ አልፎም ቢሆን ይቆጡኝ እንደነበር አስታውሳለው። እውነት ለመናገር ስገረፍ ብዙም ትዝ አይለኝም። ታድያ ሁል ግዜ በምክርም ይሁን በቁጣ መካከል የማጠፋዋ ቃል #ሁለተኛ_አይለመደኝም በል የምትለዋ ናት። እኔ ግን ሁሌ አይለመደኝም ብዬ ተመልሼ እዛው ነኝ። 

🫣

 ልጅነት አይደል?  
#አይለመደኝም የምትለውን ቃል ግን አሁን አሁን ሳስበው ምን አልባት ሰባ ያህል ግዜ ወይም ሰባት ግዜ ሰባ ያህል #ሁለተኛ_አይለመደኝም  እያልኩ #እየተለመደኝ አልፌያለው። ሁሌም  ሁለተኛ እድል ሶስተኛ የሌለው #ሁለተኛ_አይለመደኝም እንደጉድ አሳልፌያለው ። የናንተን ባላውቅም በኔ በኩል  እግዜሩም  ጋር ስመጣ ነገሩ እንደዛው ነው የቀጠለው። 
#ደግመህ_አታድርገው እኔ ግን እንደው ስንት ግዜ ደጋገምኩት አንድ አንዱንማ ኮመኮምኩት የናንተንስ አስባችሁታል ? እግዚያብሔር ግን እንዴት ያለ የሁለተኛ እድል ባለቤት ነው መሰላችሁ የትእግስቱስ ብዛት ስፍር የለውም።  ያቺን በዮሐንስ 8:11 ላይ ያለች ሴት ጌታ ኢየሱስ እንደዚህ አላት። 
እርስዋም፦ “ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ” አለች። ኢየሱስም፦ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ #ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፡” አላት።
እኔ በበኩሌ ከቤተሰቦቼም ብቻ ሳይሆን ከጌታ እራሱ የተሰጡኝ ሁለተኛ አይለምደኝሞች እጅግ ብዙ ናቸው። ስንት ግዜ ደግመህ አታድርገው ተብዬ ወዲያው እንደደገምኩት ሳስበው እራሱ ያስቀኛል። መለስ ስል ደግሞ ልጅ አይደለሁ የፍቅር ልክ የሆነው አባቴ እንደገና ይቀበለኛል። 
አሁን አሁን በአይለመደኝም ምንም አይነት ፅድቅ እንደማይሰራ በደንብ ገብቶኛል በፀጋ ብቻ እንጂ። ምክንያቱም እኔ ብዙ ተለመደኛ እንደቤተሰቦቼ ቁጣ እግዜሩም ጋር #ሁለተኛ_አይለመደኝም  ብዬ ደጋግሜ አጠፋሁ። ሁል ግዜ ሀጥያት የሚመስሉን ነገሮች ጥቂት ናቸው እና  አሁን እንኳን ይህን ፅሁፍ የምታነቡ አንድ አንድ ጓደኞቼ “መቸም ይሄ ልጅ ፈጀው“ ልትሉ እንደሆን ሳስበው ሁሉ እስቃለሁ 

ደሞ እንማን እንደሆናችሁ አውቃለው 

። ብቻ ዛሬ ስለሀጥያት ይህን አልልም ነገር ግን በእግዚያብሔር ዘላለማዊ ምሪት ውስጥ ፣ ወይንም ደግሞ ከጌታ ሰምተን ባልታዘዝናቸው ሩጫዎች ውስጥ ፣ ወይንም ደሞ ከጌታ ሰምተን ዘንግተን በረሳናቸው ራዕዮች ውስጥ ፣ ወይንም ደግሞ በሀጥያትስ ውስጥ ቢሆን እንደውም “ያበጠው ይፈንዳ”. . . . . 
– ስንት ግዜ ከአጀንዳው ወጣን 
– ስንት ግዜ በአይምሮ ባከንን
– ስንት ግዜ በጭንቀት አነጋን 
– ስንት ግዜ በፍርሀት ተዋጥን 
– ስንት ግዜ እምነት ጎደለን 
– ስንት ግዜ ስንት ሆነን አስመስለን አጠፋን 
እናንተ የናንተን ቁጠሩት የኔ ብዙ ነው ። እግዜሩ ግን ስንት ግዜ እንዳይለመዳቹህ እያለ ወደ መንገድ አስገባን። ሀምሳ አጥፍተን ሁለተኛ እያለ ያስቀጠለን አምላክ ስሙ ይባረክ። 
ዛሬ እንደው ለማስታወስ ያህል ይህን እላቹሀለው ግድ የለም ብቻ መለስ እንበል ከሀሳባችንም ፣ ከድርጊታችን ፣ልክ ከሚመስለን ሩጫችን ፣ ካስፈለገም እንኳን ሩጫ ከበዛበት አገልግሎታችን መለስ እንበል እሱ እንደሆን ሁለተኛ እድል አያልቅበት። የብሉይ ኪዳኑ ሳምሶን እንኳ በህይወት ከገደላቸው በሞቱ የገደላቸው በልጠውለት የለ። 
በሁለተኛ እድል ውስጥ መዘርጋት ፣ መስፋት ፣ መረጋጋት ፣ እረፍት እና ድል አለ።
አንድ አንድ ግዜ እግዜሩን ስንት ግዜ ሁለተኛ ልበለው የሚል መሳቀቅ እንዳይዛቹህ እሱም ሁለተኛ ብሎ  የሚመለስን በደስታ ይቀበላል ጉዞን ያስቀጥላል እንጂ ሀኬተኛ ብሎ አይጠራም ባህሪውም አይደል።
መልካም የ #ሁለተኛ_አይለመደኝም ሳምንት ይሁንላቹህ።  
#ሁለተኛ_አይለመደኝም

One Comment

Leave a Reply to A WordPress Commenter Cancel reply