Archives

Tags

ሰንበት_አይደል ?

አይሁድ መቼም ስለሰንበት ስታነሱበት እንዴት በደስታ እና ህግን በመጠበቅ እንደሚያከብረው ከነማስጠንቀቂያው እንደሚናገርም ጭምር አወቃለሁ። በአንድ ወቅት የምሰራበት NGO ውስጥ የበላይ አለቆቻችን በጌታ የሆኑ አይሁዳውያን ነበሩ እና ባህላቸውን (ሰንበታቸውን) በተደጋጋሚ ከአርብ ምሽት ጀምሮ አሳይተውናል አብረናቸውም ሰንበታቸውን ሰንበታችን አድርገን ሰንብተን እናውቃለን። በመጀመርያ የተሰጠውስ ለነሱ አይደል ?  ይህ ታድያ በየሳምንቱ አመቱን ሙሉ የሚደረግ ድርጊት ነበር። በጣም የሚወዱትንም ሰው የሚጋብዙት እዚህ ድግሳቸው ላይ እንደነበር አይቻለው። አምላካቸውም ቢሆን ሰንበትን አርፎአል ምን እነሱ ብቻ።

ሰንበት ህግ ነው።
ሰንበት እረፍት ነው።
ሰንበት ሸክምን ማራገፊያ ቀን ነው።
ሰንበት ከግብፅ ምድር ላወጣህ አምላክ መታሰቢያ ነው።
ሰንበት አምላክን ማሰብያ ቀን ነው የተለየ ቀን ሁሉ ተረስቶ እሱ ብቻ የሚታወስበት የከበረ የእረፍት ቀን። በዙርያቸው ያሉ አንድም ህዝብ የማያከብሩት ለነሱ ብቻ የተሰጠ ልዩ ቀን ነው። በማክበራቸው ውስጥ የአምላካቸው ደስታ አለ የህግ ፍፃሜ እና አደረኩት የሚል የፍፅምና ደስታም አለው። በረከትም አለው እንደቃሉ ባከበሩት ሁሉ አልከሰሩም ተባረኩ እንጂ አንድም አላጎደሉም በሙላት ተትረፈረፉ እንጂ። ታድያ በባለፈው ኪዳን መሆኑን ልብ ይሏል።

#የሰው_ልጅ_ለሰንበት_ጌታዋ_ነው

ማቴዎስ 12:8፤ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።”

ይህን ቃል ኢየሱስ እስኪናገረው ድረስ ሁሉ ልክ ነበር ሰንበት እረፍት ነበር በብዙ መቅበዝበዝ ውስጥ ያለች የሰላም ጥማት የምታሳልፍ እርካታን ያልታደለች ቀን። ሰንበት ቀን ብቻ ነበረች ሞልታ የማትሞላ በኋላ እና ከፊት ባሉ የመቅበዝበዝ ቀናቶች ውስጥ ያለች ነጋች ስትባል የምትጨልም አንዲት ቀን።

ዕብራውያን 4:9፤ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።

አሁን ግን ሰንበት እንደዚህ አይደለችም ሰንበት የዘላለም ህይወት እረፍት ናት፣ ከስራ አርፎ ወደስራ መግቢያ አይደለችም በእረፍት ውስጥ መሮጫ ፣ በሩጫ ውስጥ ያለች በቃላት የማትነገር የዘላለም ፍስሀ ናት ሰንበት አሁን ሰንበት ቀን አይደለችም ሰንበት ዘላላም ናት አንድ ግዜ ብቻ የሚገባባት አንድ በር ብቻ ያላት ከቶም የማይወጣባት መኖርያ ናት። የቀደሙቱ ብዙ ሰንበቶችን አረፉ ግን ተቅበዘበዙ አንድ ግዜም አላረፉም የማረፍ ሙከራ አደረጉ ቀኑ ሲቀየር ደሞ ተነስተው ሮጡ ደሞ ቀንዋ ስትመጣ ለማረፍ ሞከሩ እያሱ ግን አንድ ግዜ አላሳረፋቸውም ግን ሞክረዋል ያለእረፍት አርፈዋል። አሁን ግን ሰንበት በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም እረፍት ናት ፣ ድሮ ቀን ነበረች አሁን ግን ሰንበት የቀኑ ጌታ ኢየሱስ ነው በእርሱ በኩል ማረፍ ሆንዋል።
በሰንበት ይህን ፅሁፍ የምታነቡ ወዳጆቼ እናንተስ አርፋችሁ ይሆን ?? ለቀን ወይስ ለዘላለም ? በጩሀት ውስጥ ወይስ ከጩኸት በላይ የቱ ጋር ይሆን ያረፋችሁት።

ዕብራውያን 4:10፤ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።

አሁን ግን ሰንበት ቀናት እና እረፍትን ጠብቀን ቤት ቁጭ ብለን የምናሳልፋት አይደለችም ፣ ደጀ ሰላም ሄደን ተሳልመን የምንመጣትም አይደለችም። ትክክለኛው የሰንበት እረፍት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ያለ እረፍት ነው። እዛ ሰንበት ውስጥ ፈውስ አለ የአይምሮ ሰላም አለ እዛ ሰንበት ውስጥ አምላክ አለ አምልኮውም አይጓደል። እንግዲያውስ  ቀኑን ሳይሆን የቀኑን ባለቤት እርሱንሚያሳርፈውን መገናኘት ይሁንልን። ቀኑን አክብረን የተሰጠንን የዘላለም እረፍት የሆነንን ኢየሱስን ካላገኘነው አርፈው በቁጣው እንዳይገቡ ከተደረጉት እኩል መሆናችን አይደል ስለዚህ ወደዚህ እረፍት በመግባት ከሩጫችን ፣ ከራሳችንም ፣ ከምድር ዝባዝንኬም እልፍ ብለን አምላካዊውን እረፍት ማረፍ ይሁንልን።

መልካም #ሰንበት።

3 Comments

  • Stefan

    August 2, 2019 at 11:46 am

    At quo quodsi sanctus accumsan. Soleat eligendi corrumpit et vim, cu alterum maluisset mel. Et ignota int gream cum. Eu sit noster dolores. Nam an essent eloquentiam.

    Reply
  • Silvia

    August 2, 2019 at 11:47 am

    Ut exerci consequat cum, in quo nemore viderer luptatum, mei no regione dolorum. Ea per idque simul, in estsit referrentur, epicurei omittantur sed ne. Errem interesset ut est, vim no simul consequat.

    Reply
  • David

    August 2, 2019 at 11:48 am

    Quod iriure has ex. Ut ferri persequeris duo. Deserunt patrioque ex est, per oportere disputando ad.udiandame suscipiantur an per. Mazim iusto semper ut vel mei ea diam liber.

    Reply

Leave a Reply to Stefan Cancel reply