ዮሐንስ ወንጌል 4:40
የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ለመኑት፤ በዚያም #ሁለት_ቀን ያህል ኖረ።
ይህ ክፍል ኢየሱስ በሰማርያ አንዲትን ሴት ካዋራ እና ብዙ የአንድ ቀን ተአምራት ካደረገ በኃላ የሰማርያ ሰዎች እንዲቆይ እንዲከርም የጠየቁት ክፍል ያለበት ነው። ይቺ ከተማ ሁሌም በጣም ትገርመኛለች። ሰዎቹ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየሱስ በመምጣት እና በመጠየቅ ከሚሄድበት ጉዞ ዘግየት አድርጐ ቢፈልግ ኖሮ እንዲያስተምር እንዲፈውሳቸው ነው የጠየቁት እርሱስ ደግ አየደል ተለመናቸው እና ኑር የሚለውን ጥያቄያቸውን በሁለት ቀናት ቆይታ አሳጥሮ እነሱን ሆኖ እነሱን መስሎ የነሱን በልቶ አብሮአቸው ከነደቀመዛሙርቱ ከረመ ደግ ኢየሱስ።
በጣም ደስ የሚለኝ ሀሳብ ሁል ግዜም “ማኖር” የሚለው ሀሳብ ነው አንድ ግዜ አንድ ጓደኛዬ ሲሰብክ እንደዚህ አለ Ab Hailu መንፈስ ቅዱስ እኛ ጋር ሲመጣ የሚመጣው ለጉብኝት (visitation) ሳይሆን ለመከተም አብሮ ለመኖር (habitation) ነው”። እንዴት ያለ መረዳት ነው ይሄ ? ሳምራውያንስ ምን አይነት ህዝቦች ይሆኑ ?? መጎብኘትን ሳይሆን ማኖርን የሚመርጡ።
እነዚህ የሰማርያ ሰዎች አስር ከተማ ከሚባለው ከጌርጌሶን አገር ሰዎች እጅግ ይለያሉ። እነዚያ ያስቸገራቸውን ያቃታቸውን ያስጨነቃቸውን ነገር ስለፈታላቸው ከከተማቸው እንዲወጣላቸዉ እንዲሄድ ለመኑት እነዚህ ደሞ ጉዳቸውን ነግሮአቸው መተባበር ከማይችላቸው ከሚጠሏቸው ከሚጠየፏቸው ከአይሁዳዊያን ወገን እንደሆነ እያወቁ እንዲቆይ ለመኑት።
እኛ ከየትኛዎቹ እንሆን ?? መጥቶ ቤት ጓዳችንን ሲያተረማምሰው እና እርያ የሆኑቱን ግን የምንወዳቸውን ጉድፎቻችንን ሲያስወጣልን የምንከፋ አልያም ውጣልን ባንለው እንኳ ጥለነው የምንሄድ ወይስ እነሱ ወጥተዋል በል ደሞ አንተ ግባ በእልፍኜ ኑርበት የምንል ?? የትኛው ነን እኛ ለእግሩ ውሃ የምናቀርብ ወይስ በሽቶ የምናጥበው ?
እርሱ ትንሽዋን ይፈልጋል እና ዛሬም ትንሽዋን ልባችንን እንስጠው መቼስ ቤት አይበቃው እርሱ እጅግ ትልቅነው። መልሳችንም ጥያቄያችንም በእልፍኝ ያምራልና በዛ ኑር እንበለው።
#ሁለት_ጣፋጭ_ቀናት


